በጋምቤላ ክልል የኢሬቻ በዓል በመልካ ባሮ በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል፡፡
በክልሉ በጋምቤላ ከተማ ኢሬቻ "መልካ ባሮ" ሲከበር የዘንድሮው ለ5ኛ ጊዜ ነው፡፡
ኢሬቻ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠውና ፈጣሪን ለማመስገን በየዓመቱ የሚከበር ታላቅ በዓል ነው፡፡
በጋምቤላ ከተማ እየተከበረ በሚገኘው የኢሬቻ በዓል አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች እንዲሁም ቄሮና ቀሬዎችን ጨምሮ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡