የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) ከፍተኛ ምክትል ፕሬዚዳንት ናኦኪ አንዶ ጋር በሁለትዮሽ የልማት ትብብር ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
አቶ አህመድ በውይይቱ ወቅት ጃፓን ባለፉት ዓመታት ለኢትዮጵያ የልማት ጥረት ላሳየችው አጋርነት እና ላበረከተችው ወሳኝ ድጋፍ አመስግነዋል።
በተለይም እንደ መሠረተ ልማት፣ ኢነርጂ እና ኢንዱስትሪ ባሉ ዘርፎች እያደገ የመጣውን የኢትዮጵያ የልማት ፍላጎት ለማርካት ጃፓን ድጋፏን አጠናክራ እንድትቀጥል ጠይቀዋል።
ሚስተር ናኦኪ አንዶ በበኩላቸው፥ ጃይካ በተለይ ኢንቨስትመንት በመሳብ፣ በግሉ ዘርፍ ልማት እና በኢንዱስትሪ ሽግግር ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የአጋርነት ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በቢታንያ ሲሳይ
#ebcdotstream #ethiopia #japan #jica