የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የመግቢያ ነጥብ ይፋ አደርጓል።
በ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና ወስደው ትምህርታቸው በቴክኒክና ሙያ የትምርህርት ተቋማት ለሚከታተሉ ተማሪዎች የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ደረጃ 1 እና 2፣ ደረጃ 3 እና 4 እንዲሁም ደረጃ 5 በሚል የተከፈለ መሆኑን የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ተሻለ በረቼ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
በዚህም መሠረት:-
ለደረጃ 1 እና 2 የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ለወንዶች - 134 በታች ለሴቶች 121 በታች፤ ለወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 132 በታች ለሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 120 በታች፤ ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች - 120 በታች ተደርጓል።
ለደረጃ 3 እና 4 የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ለወንዶች -135 እና ከዚያ በላይ በታች ለሴቶች 122 እና ከዚያ በላይ፤ ለወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 133 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎች -121 ከዚያ በላይ፤ ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 121 እና ከዚያ በላይ።
ለደረጃ 5 ለወንዶች 179 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች - 168 ከዚያ በላይ፤ ለወንዶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 168 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች አርብቶ አደር አካባቢዎች 157 እና ከዚያ በላይ፤ ለሁሉም ክልል አካል ጉዳተኞች 142 እና ከዚያ በላይ ሆኗል።
በተዘጋጀው የመቁረጫ ነጥብ መሠረት በትምህርት ስልጠና ዘመኑ 454ሺህ 106 ተማሪዎች ሙያ ዘርፋን ይቀላቀላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሚኒስትር ዴኤታው በመግለጫቸው አንስተዋል።
በኤዶምያስ ንጉሴ