Search

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሥርዓተ ቀብር ተፈፀመ

ሰኞ ጥቅምት 10, 2018 65

የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ሥርዓተ ቀብር በኑዛዜያቸው መሠረት በአዲስ አበባ ዛሬ ተፈፅሟል።
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በአጋጠማቸው ድንገተኛ ሕመም ምክንያት የሕክምና ክትትል ሲያደርጉ ቆይተው ጥቅምት 9 ቀን 2018 በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ኢትዮጵያውያን ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በሕይወት ዘመናቸው የሚታወቁበትን “የሰው ልጅነት ይቀድማል” አስተምህሮ የዘወትር መመሪያ እንዲያደርጉት ጥሪ ቀርቧል።
በላሉ ኢታላ