በተከናወኑ ሰው ተኮር ሥራዎች በጎ አድራጎትን ከውጭ ዜግነት እና እርዳታ ጋር የማያያዝ ትርክትን መቀልበስ ችለናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
“መስጠት አያጎድልም፣ በጎ ፈቃደኝነት ለሀገር ማንሰራራት” በሚል ለ2017 ዓ.ም በጎ ፈቃደኞች የእውቅና እና የሽልማት መርሐ-ግብር ተካሂዷል።
ባለፉት 7 ዓመታት 42.5 ቢሊዮን ብር የሚገመቱ የበጎ አድራጎት ሥራዎች የተከናወነ ሲሆን፤ ከ40 ሺህ በላይ የአቅመ ደካሞች ቤቶችን ማደስ ተችሏል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

በተጠቀሰው ወቅት በተደጋጋሚ በተከናወነ የማዕድ ማጋራት ሥራም ከማዕድ ባሻገር ፍቅርን ማጋራት እንደተቻለም ከንቲባ አዳነች አክለዋል።
በ2017 ዓ.ም ብቻ 16.1 ቢሊዮን ብር የሚገመቱ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸው፤ ግለሰቦች፣ ባለሀብቶች፣ ተቋማት፣ ሲቪክ ማኅበራትን ጨምሮ ይህ እንዲቻል ላደረጉ በጎ አድራጊዎች ምስጋና አቅርበዋል።
አዲስ አበባ ከበጋ እስከ ክረምት እየሰጠችው ባለው የበጎ አድራጎት አገልግሎት በሀገሪቱ ካሉ ክልሎች ባለፈ በአፍሪካ ላሉ 15 ሀገራት ምርጥ ተሞክሮዋን እያካፈለች ስለመሆኑም ተገልጿል።
በሰናይት ብርሃኔ
#ebcdotstream #addisababa #communityservice #socialresponsibility