Search

በባሕርዳር እየተነቃቃ ያለው የቱሪዝም እንቅስቃሴ

ረቡዕ ጥቅምት 12, 2018 34

ባሕርዳር ከተማን ዓለም አቀፍ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታውቋል።
የመምሪያው ኃላፊ አቶ ጋሻው ከኢቲቪ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ከተማ አስተዳደሩ የጣና ሐይቅ ውበትን የመግለጥ፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን የመደገፍ፣ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ የቅርስ ጥገናና የተለያዩ ኮንፈረንሶችን በማካሄድ የቱሪዝም እንቅስቃሴውን ማነቃቃት መቻሉን ገልፀዋል።
ከተማዋ አሁን ላይ ሰላማዊ በመሆኗ ለኮንፈረንስ፣ ለሐይማኖታዊ እና ለንግድ ቱሪዝም ተመራጭ ሆናለች ብለዋል።
በዚህም ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ ከ700 በላይ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች እና ከ100 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ጎብኝዎች ባሕርዳርን በመጎብኘታቸው፣ ከ103 ሚሊዮን ብር በላይ ወደኢኮኖሚው ፈሰስ ሆኗል ሲሉ አስረድተዋል።
በባሕርዳር ከተማ ከሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች መካከልም የጢስ ዓባይ ፏፏቴ፣ የአፄ ፋሲል ድልድይ፣ የቤዛዊት ኮረብታማ ስፍራ፣ የዘጌ ባሕረገብ ምድር፣ የጣና ደሴቶች ፣የተለያዩ ጥንታዊ ቅርሶች እንዲሁም የጣና ዳር የኮሪደር ልማት ሥራዎች ዋናዎቹ መሆናቸው ተመላክቷል።
በተስፋሁን ደስታ