ከጠንካራ ሥራ በኋላ አሁን የኮይሻ ግድብ 128 ሜትር ከፍታ ላይ መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ይህ ኮይሻ የደረሰበት ከፍታ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አሁን ላለበት የ145 ሜትር ከፍታ 17 ሜትር ብቻ የቀረው እንደሆነ ጠቅሰዋል።
ያኔ ሕዳሴ ቁፋሮን ጨምሮ በርካታ የተጀመሩ ሥራዎች እንደነበሩት የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኮይሻ ግን ከባዶ ጀምሮ እዚህ መድረሱን ገልጸዋል።

ለሀገራቸው የቆሙ ኢትዮጵያውያን ቀን እና ሌሊት በመሥራት ፕሮጀክቱን እዚህ ደረጃ ላይ ማድረሳቸውን ጠቅሰው፣ ከኢትዮጵያውያን ኅብረት እና ትብብር ውጪ ገንዘብ ስላለ ብቻ ይህን የመሰለ ሥራ እንደማይሳካ ተናግረዋል።
ፕሮጀክት ሲሠራ የአካባቢው ማኅበረሰብ ተሳትፎ ከሌለበት ውጤታማ እንደማይሆን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ለኮይሻ እዚህ መድረስ የአካባቢው ማኅበረሰብ ተሳትፎ የሚመሰገን እንደሆነ ገልጸዋል።
በሥራው ሂደት ኢትዮጵያ በርካታ ባለሙያዎች ያገኘችበት እንደሆነ እና ይህ ደግሞ የትም የማይገኝ ታላቅ ሀብት እንደሆነ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያወሱት።
በለሚ ታደሰ
#EBC #EBCdotstream #PMOEthiopia #AbiyAhmedAli #Koysha #dam