Search

የመደመር አንቀጽ

ዓርብ ሰኔ 19, 2018 56

 

ከአንድ ትውልድ ተሻጋሪ ሆነው የሚቀጥሉ ጠባዮችና ልማዶች ሀገራዊ እሴቶች ይሆናሉ።

ሀገራዊ እሴቶች በትውልዶች ውስጥ የማይቀያየሩ የትናንትም የዛሬም ትውልድ መገለጫና ማንነት ናቸው።

ሀገራዊ እሴቶችና ባህሎች የሚፈጠሩት በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ ነው።

በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ የጠባይና የባህል መወራረስ አለ።

ለምሳሌ ሀገርን ከጠላት የመከላከል በየዘመናቱ የነበሩ ኢትዮጵያውያን የጋራ መገለጫ እሴት ነው።

በየትውልዱ ሀገራችን ኢትዮጵያ የጠላት ወረራና የሕልውና አደጋ ይገጥማታል።

ነገር ግን ሁሉም ትውልድ ጠላትን መክቶ ሀገር ሳትደፈር ለቀጣይ ትውልድ አስተላልፏታል።

ይኸም ሀገራችን በዓለማችን ተደፍረው እና በጦር ግንባር ተሸንፈው ከማያውቁ ጥቂት ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ አድርጓታል።

የመደመር ትውልድ

ገጽ- 24