ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በነገው ዕለት ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ።
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ይካሄዳል።

በመደበኛ ስብሰባው ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ም/ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከም/ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ።
ምክር ቤቱም የመንግሥትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በዕለቱ በሚካሄደው የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ ተጠሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙ ሲሆን የስብሰባው ሙሉ ሂደትም በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የሚተላለፍ መሆኑን ምክር ቤቱ አስታውቋል።
#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #PMAbiy