Search

ኢትዮጵያውያኖች ለዓላማቸው መቆም መታወቂያቸው ነው - አምባሳደር ቲቦር ናዥ

ዓርብ ጥቅምት 21, 2018 47

የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ አምባሳደር ቲቦር ናዥ ኢትዮጵያውያኖች ለዓላማቸው መቆም መታወቂያቸው ነው ሲሉ  ገለፁ፡፡

አምባሳደር ቲቦር ናዥ ኢትዮጵያ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ጀምራ መጨረስ እንደምትችል ለዓለም አሳይታለች ብለዋል።

በህብረት እና በአንድነት መንፈስ የተሰሩ ስራዎች ለሀገሪቱ የወደፊት ተስፋ መስፈንጠሪያ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያውያን ለዓላማቸው መቆም መታወቂያቸው ነው ያሉት አምባሳደር ቲቦር ናዥ፤ በፈተናዎች መፅናት እና ጀምሮ መጨረስንም ለዓለም እያሳዩ ያሉ ህዝቦች ናቸው ብለዋል፡፡

አንዳንድ አካላት የኢትዮጵያን ግልፅ የልማት ፍላጎት በመካድ የሚያራምዱትን የቀኝ ግዛት ዕሳቤዎች በመተው ለጋራ ተጠቃሚነት መቆም እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡ 

አሁናዊ የጂኦፖለቲካ አካሄዶች ይህን ሰጥቶ የመቀበል መርህ እንደሚደግፉም አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን በጋራ አንድን ግብ ዓላማዬ ብለው ከያዙት ያንን ዕውን ከማድረግ የሚያቆማቸው ኃይል የለም ያሉት አምባሳደር ቲቦር ናዥ፤ በዲፕሎማትነት ዘመናቸው ይህን እውነት ለመመልከት መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia