Search

ኢትዮጵያ የምትጠይቀው የነበራትን የባሕር በር ነው - ብርጋዴል ጄኔራል ዋሲሁን ንጋቱ

እሑድ ጥቅምት 23, 2018 76

ኢትዮጵያ አሁን ላይ እየጠየቀች ያለው የባሕር በር ጥያቄ ቀድሞ የነበራትን ነው ሲሉ የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊት አባል ብርጋዴል ጄኔራል ዋሲሁን ንጋቱ ገለፁ፡፡

ብርጋዴል ጄኔራል ዋሲሁን ንጋቱ ከኢቲቪ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢትዮጵያ የባሕር በርን ያጣችበት መንገድ የህግ አግባብን ያልተከተለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባህር በር ይገባኛል ጥያቄዋን ለሚመለከተው ማህበረሰብ ማቅረቧንና ከ120 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ሀገር ተዘግታ መኖር እንደማትችል መግለፃቸውን ጀኔራሉ አንስተዋል፡፡

ብርጋዴል ጀነራል ዋሲሁን ንጋቱ አክለውም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሰላም እና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ አስፈላጊ በሆነ ወቅት ሁሉ ለሀገር ዘብ የቆመ የሐገር ህልውና ጋሻና መከታ ነው ብለዋል፡፡

መከላከያ ሰራዊት በግንባር ቀደምትነት በመሰለፍ የኢትዮጵያን ህዝብ የሚጠብቅ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ያሉብንን ችግሮች በሰላማዊ መንገድና በውይይት መፍታት የኢትዮጵያን ፍላጎት ለማስከበር ወሳኝ መሆኑንም ብርጋዴል ጀኔራል ዋሲሁን ንጋቱ ተናግረዋል፡፡

በንፍታሌም እንግዳወርቅ

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #national_interest #seaaccess