Search

የሶሪያው ፕሬዝዳንት በአሜሪካ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

እሑድ ጥቅምት 23, 2018 63

የሶሪያ ፕሬዝዳንት አህመድ አል ሻራ በህዳር ወር መጀመሪያ ላይ በአሜሪካ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ቀደም አንድም የሶሪያ መሪ በአሜሪካ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ባለማድረጉ ፕሬዝዳንት አህመድ አል ሻራ የመጀመሪያው መሪ እንደሚሆኑም ተመላክቷል፡፡

ፕሬዝዳንት አህመድ አል ሻራ በዋሽንግተን ዲሲ በሚያደርጉት ጉብኝት በሶሪያ መልሶ ግንባታ ዙሪያ ከአሜሪካ ባለስልጣንት ጋር እንደሚወያዩ የሶሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሳድ አልሻይባኒ አረጋግጠዋል።

ጉብኝቱ በሶሪያ ላይ ተጥለው የነበሩ ማዕቀቦችን ለማንሳትና በአሜሪካ እና ሶሪያ ግንኙነት መካከል አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት እንደሚያስችል ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

በሁለቱ ሀገራት መካከል በጣም ጠንካራ አጋርነት መመስረት እንፈልጋለን ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ የፕሬዝዳንት አህመድ አል ሻራ ጉብኝት ይህን ለማሳካት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሶሪያ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ቶም ባራክ፤ ፕሬዝዳንት አህመድ አል ሻራ በዋሽንግተን የሚያደርጉት ጉብኝት በፈረንጆቹ ህዳር 10 አካባቢ ሊሆን እንደሚችል መግለጻቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

#ebc #ebcdotstream #Syria #America