የሦስቱ ሰርጦች ፕሮጀክት በቻይና ሁቤይ ግዛት ውስጥ ከዪቻንግ ከተማ በስተምዕራብ በያንግዜ (ቻንግ ጂያንግ) ወንዝ ላይ የተገነባ በዓለም ላይ ትልቁ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ግድብ ነው።
ግንባታው በ1994 ተጀምሮ በ2012 ሙሉ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ፕሮጀክት ወደ 600 ኪ.ሜ. ስፋት የውኃ ማጠራቀሚያ፣ 2 ሺህ 335 የጎን ርዝመት፣ 185 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን፣ በተደጋጋሚ አካባቢውን በሚያጠቃው ጎርፍ ምክንያት ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከዚያ አካባቢ ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወሩ ተደርገዋል።
ባለ አምስት ደረጃ መንትያ የመርከብ መልሕቅ እና 34 ቱርቦ ጄነሬተሮች እንዲሁም 22.5 ሚሊዮን ኪሎዋት (22 ሺህ 55 ሜጋ ዋት) አቅም ያለው አጠቃላይ የውኃ መቆጣጠሪያ ሥርዓት አለው።
ፕሮጀክቱ በያንግዜ ወንዝ ላይ በጎርፍ ቁጥጥር፣ በኃይል ማመንጫነት፣ በውኃ አቅርቦት እና በማጓጓዣ ሁለገብ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
ፕሮጀክቱ ከላይኛው ተፋሰስ ጋር በቅንጅት በመሥራት ከ29 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ የጎርፍ ውኃ በማስቀረት በአካባቢው አደጋ ሲፈጥር የነበረውን ጎርፍ ማስቀረት ችሏል።
ከ423 ቢሊዮን ኪሎዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት 128 ሚሊዮን ቶን የድንጋይ ከሰልን በማስቀረት የካርቦን ልቀትን በ347 ሚሊዮን ቶን የቀነሰ ንጹህ የኃይል ምንጭ ተምሳሌት ነው።
ፕሮጀክቱ ለታችኛዎቹ የተፋሰስ ክልሎች በድርቅ ወቅት 82.4 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ መልቀቅ የኢንዱስትሪ፣ የቤት ውስጥ እና የሥነ-ምህዳር ፍላጎቶችን እያሟላ ይገኛል።
ከ2023 ጀምሮ ዓመታዊ የማጓጓዝ አቅሙን ወደ 150 ሚሊዮን ቶን ያሳደገው ፕሮጀክቱ፣ እስካሁን ከ700 ሚሊዮን ቶን በላይ ጭነቶችን በማጓጓዝ ከክልል ወደ ክልል የሚደረገውን የጉዞ ቅልጥፍና ማሳደጉም ነው የተጠቀሰው።
እንደ ፈጣን የመተላለፊያ ኮሪደር ሆኖ የሚያገለግለው ግድቡ በመርከብ ብቻ ከ1.7 ሚሊዮን በላይ መንገደኞችን ያጓጓዘ ሲሆን፣ 15 ሚሊዮን ቶን ጭነትም ማጓጓዙንም የሲጂቲኤን መረጃ ያመላክታል።
በለሚ ታደሰ