የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ የሐሳብ ልዕልናን በጦርነት ማምጣት እንደማይቻል መታወቅ አለበት ብለዋል።
ኢትዮጵያዊያን ላለፉት ዓመታት የችግር መፍቻ መንገድን በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ በሚገባ መገንዘባቸውን ከኢቲቪ ዜና ኢትዮጵያ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።
የሐሳብ ልዕልናን ለማረጋገጥ ሕዝቦች ተባብረው እና ተደማምጠው መግባባት ላይ የሚደርሱበት አካሄድ ሊኖር እንደሚገባ ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያዊያን አንድ የሚያደርጓቸው ባህሎች፣ ትውፊቶች እና እሴቶች እንዳሉ ሆኖ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የሚለያዩአቸው ግጭቶች እየተፈጠሩ ስመሆናቸው አንስተዋል።
ይህንንም ችግር ለመፍታት ሁሉምን የኅብረተሰብ ክፍል ያካተተ ውይይት ለማድረግ የውይይት ርዕሰ ጉዳዮቹን የመለየት ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል።
የአንጀንዳ ማሰባሰብ ሥራው ተጠናቅቆ የጋራ መግባባት ላይ ከተደረሰ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ መፃኢ ዕድል በእኩልነት አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ነው የጠቀሱት።
ችግሮችን በመነጋገር መፍታት እንደሚቻል እስካሁን ያየናቸው የምክክር ሂደቶች አሳይቶናል ብለዋል ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ።
የሀገሪቱ ዴሞክራሲ እንዲያብብ ከተፈለገ ሁሉም ዜጎች እኩል መብት ኖሯቸው በሀገራቸው ጉዳይ በነፃነት ሐሳባቸውን ሊገልጹ ይገባልም ነው ያሉት።
ሀገራዊ ምክክሩ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን አሸናፊ እንደሚያደርግም ተናግረዋል።
በሜሮን ንብረት
#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #NationalDialogue