ባለፉት 3 ወራት ብቻ ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ቱሪስቶች የአማራ ክልልን መጎብኘታቸው ተገለፀ፡፡
የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛውን ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ገምግሟል።
በዚህም ባለፉት 3 ወራት ብቻ ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ቱሪስቶች የአማራ ክልልን እንደጎበኙ አስታውቋል፡፡
ክልሉን ከጎብኙት ቱሪስቶች ውስጥ 31 ሺህ የሚሆኑት የውጭ አገር ዜጎች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
ክልሉ በሩብ ዓመቱ ብቻ ከቱሪስቶች ገቢ 2.4 ቢሊዮን ብር ማገኘት እንደቻለም ተገልጿል፡፡
የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በርካታ ኃይማኖታዊና ህዝባዊ ክብረ በዓላት የተከናወኑበትና ሁነቶቹም የበዙበት ሲሆን፤ ሁሉም በዓላት በልዩ ድምቀት መከበራቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መረጃ አመልክቷል።
#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #Amhara #Tourism