የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ "እንዳይደገም መቼም አንረሳውም" በሚል መሪ ቃል በሚከበረው የሰሜን ዕዝ ዝክረ ሰማዕታት መታሰቢያን አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ሠራዊት በተሰማራበት ግዳጅ መስዋዕትነት ያለ እና ወደፊትም የሚቀጥል መሆኑን የጠቀሱት ኢታማዦር ሹሙ፣ "የሰሜን ዕዝን መስዋዕትነት ልዩ የሚያደርገው በኢትዮጵያ ታሪክ ምናልባትም በዓለም ታሪክ የመጀመሪያው መሆኑ ነው" ብለዋል፡፡
ዕለቱን የምናስታውሰው እንዳይደገም ነው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ "ሰሜን ዕዝ ከተመታ ጊዜ ጀምሮ እንቅልፍ ከልብ ወስዶን አያውቅም" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
"እኔ በግሌ ዕድሜ ልኬን የማልረሳው እና በሕይወቴ በጣም የደነገጥኩት በሰሜን ዕዝ መመታት ነው" ያሉት ኢታማዦር ሹሙ፣ ጉዳዩን የከፋ የሚያደርገው ደግሞ በባዕድ ሳይሆን በወገን መሆኑ ነው ብለዋል፡፡
ባዕድ ቢሆን ያጋጥማል ተብሎ እንደሚታለፍ ጠቁመው፣ ወገን ከመክዳት አልፎ ሲጨክንብህ ግን ስብራት ሆኖ ይኖራል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በለሚ ታደሰ
#EBC #ebcdotstream #ENDF #NorthCommand #Ethiopia