Search

የትግራይ ህዝብ በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን ክህደት አይቀበለዉም - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

ሰኞ ጥቅምት 24, 2018 41

የትግራይ ህዝብ በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን ክህደት አይቀበለዉም ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለፁ።

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ "እንዳይደገም መቼም አንረሳውም" በሚል መሪ ቃል በሚከበረው የሰሜን ዕዝ ዝክረ ሰማዕታት መታሰቢያን አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በማብራሪያቸው፤ ሰሜን ዕዝ የተከዳው ኢትዮጵያን ለመጠበቅ ቃል ኪዳን ገብተው በአንድ ሌሊት ቃላቸውን ባጠፉ ከሃዲዎች ነው ብለዋል፡፡

ስለዚህ ክህደት እና አስናዋሪ ታሪክ ስናውራ ስለ ጥቂት የሕወሓት አመራሮች እንጂ ስለ ትግራይ ሕዝብ አይደለም ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ፣ "የትግራይ ሕዝብ በልጆቹ ክህደት አፍሮ፤ ተመልሰን መቐለ ስንገባ አጨብጭቦ ተቀብሎን ነበር" ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ሕዝብ መቼም ቢሆን ከሃዲ ሊሆን እንደማይችል ጠቅሰው፤ ከሕዝብ የወጡ እነዚህ ከሃዲዎች ግን 50 ዓመታት በፊት ጀምሮ ኢትዮጵያ ላይ ክህደት ሲሠሩ እና ሀገሪቱን የባሕር በርም እንደሳጧት ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ የዐርበኞች ሀገር ብትሆንም ባንዳዎችም በየዘመኑ ኢትዮጵያ ላይ በተሞከሩ የውጭ ወረራዎች መታየታቸውን አስታውሰው፣ በመገናኛ እጥረት የጥንቱ ባንዳ ምን እንደሠራ በዝርዝር ባይታወቅም የዛሬው ግን እያንዳንዱ በግልጽ እንደተቀመጠ ገልጸዋል፡፡

በለሚ ታደሰ

#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #ENDF #NorthCommand