የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ "እንዳይደገም መቼም አንረሳውም" በሚል መሪ ቃል በተከበረው በ5ኛ ዓመት የሰሜን ዕዝ ዝክረ ሰማዕታት መታሰቢያ ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በንግግራቸውም፤ "ምንም ብንታገስ ከተጠቃን መከላከላችን አይቀርም ጦርነትን እኛ ብቻ ማስቀረት አንችልም" ብለዋል፡፡
መንግሥት ሁልጊዜም ለሰላማዊ መንገድ በሩን ክፍት ማድረጉን ጠቁመው፤ ከትላንት ባለመማር የሚደረግ ፉከራ መቆም አለበት ሲሉ ተናግረዋል።
የባንዳ ስራ ላይ የተሰማሩና ህዝቡን የማይወክሉ ኃይሎች ከሀገር ክህደት ተግባራቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባም ገልፀዋል።
ጦርነት አንፈልግም በልማታችን ላይ የመጣውን ግን መመከት አለብን፤ የታጠቅነውም ለዚህ ነው ብለዋል ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፡፡
ሞትና መስዋትዕነት በሰሜን ዕዝ አልተጀመረም ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ መከላከያ ሰራዊት እየሞተና መስዋትነት እየከፈለ ሀገር ማቆየቱን ጠቅሰዋል፡፡
ሰሜን ዕዝ ከ20 ዓመታት በላይ ዳር ድንበር በመጠበቅና በልማት ለትግራይ ህዝብ ባለውለታ የነበረ ሠራዊት እንደነበርም አውስተዋል፡፡
የሰሜን ዕዝ ጥቃት መቼም እንደማይረሳ ገልጸው፤ ቀኑ የሚዘከረው መቼም እንዳይደገም መሆኑን አንስተዋል።
#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #ENDF #NorthCommand