➡️ መከላከያ ሠራዊት ሕይወቱን ከሰጠለት ሕዝብ ውስጥ የወጡ ጥቂት ካሃዲዎች ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ከኋላው መውጋታቸው ሕመሙ ጥልቅ ነው
➡️ በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈፀመው ክህደት ወንድም ወንዱሙ ላይ የፈፀመው ክህደት በመሆኑ በታሪክ ልዩ ያደርገዋል
➡️ የመከላከያ ሠራዊት የአሸናፊነት ምሥጢር የአባቶቹን አርበኝነት መውረሱ ነው
➡️ የኢትዮጵያ ገዢ ባሕሪው የአርበኝነት ቢሆንም ሀገሪቱ ባንዳም ነበራት፣ አላትም
➡️ የትግራይ ሕዝብ በሰሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመውን ክህደት አይቀበለውም
➡️ የትግራይ ሕዝብ በልጆቹ ክህደት አፍሮ፣ ተመልሰን መቐለ ስንገባ አጨብጭቦ ተቀብሎን ነበር
➡️ ስለዚህ ክህደት እና አስናዋሪ ታሪክ ስናውራ ስለ ጥቂት የሕወሓት አመራሮች እንጂ ስለ ትግራይ ሕዝብ አይደለም
➡️ ይህ ጉጅለ በሻዕቢያ ተቀጥሮ ሀገር ያስገነጠለ እና የባህር በር ያሳጣን ነው
➡️ የትግራይ ወንጀለኛው ጉጅለ የትግራይን ሕዝብ ዕጣ ፈንታ መወሰን የለበትም
➡️ የትግራይ እናት ልጇን ለጦርነት ሰጠች የሚለው የህወሓት ትርክት የተሳሳተ ነው፤ እናት ልጄ ይሙት ብላ ወደ ጦርነት አትልክም
➡️ እኛ ጥያቄያችን አሁን አድጓል፤ ይታፈን የነበረው የባህር በር ጥያቄ ወደ ፊት መጥቷል
➡️ መከላከያ ሠራዊት የሚዋጋው ለሥልጣን አይደለም፤ እኛ እዚህ ያለነው አባቶቻችን የሰጡንን ሀገር ለልጆቻችን ለማስተላለፍ ነው
➡️ አንቸኩልም፤ ጦርነት አንፈልግም፤ አንቀሰቅስም። በልማታችን ላይ የመጣውን ግን መመከት አለብን፤ የታጠቅነውም ለዚህ ነው
#EBC #ebcdotstream #ENDF #NorthCommand #martyr