Search

ላሚን ያማልን የዓለም ውዱ ወጣት ተጫዋች ያደረገው የስፖርት ጥናት

ዓርብ ጥቅምት 28, 2018 41

የእግር ኳስ ተጫዋቾችን የዝውውር ዋጋ እና በሚሰጡት አገልግሎት መሰረት የዋጋ ግምታቸውን የሚያወጣው 'ሲአይኢኤስ ፉትቦል አብዘርቫቶሪ' (CIES Football Observatory) ከስፖርት ጥናቶች ማዕከል ጋር በጋራ በአካሄዱት ጥናት ከ20 ዓመት በታች የሆኑ ወጣት ተጫዋቾችን ወቅታዊ የዝውውር ዋጋ ይፋ አድርገዋል።
ስፔናዊው የባርሴሎና አጥቂ በወቅታዊው የወጣት እግር ኳስ ተጫዋቾች ዋጋ 308 ሚሊዮን ፓውንድ እንደሚያወጣ ተገምቷል።
በዚህም መሰረት ከሁለት ዓመት በፊት የፕሮፌሽናል ጨዋታውን ለካታላኑ ክለብ ማድረግ የጀመረው የ18 ዓመቱ ላሚን ያማል የዓለማችን ውድ ዋጋ ያለው ወጣት ተጫዋች በመሆን ቀዳሚ ሆኗል።
የቼልሲው ኤስቴቫኦ በ104 ሚሊዮን ፓውንድ፣ የባርሴሎናው ፓው ኩባርሲ በ99 ሚሊዮን ፓውንድ፣ የማድሪዱ ፍራንኮ ማስታንቱኖ በ90 ሚሊዮን ፓውንድ እና የፒኤስጂው ዋረን ዛየር ኤመሪ በ81.2 ሚሊዮን ፓውንድ የዝውውር ዋጋ ግምት፣ ከሁለተኛ እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
 
በአዲስ የሺዋስ