Search

ሚካኤል ሜሪኖ ሁለት ግብ ባስቆጠረበት ጨዋታ አርሰናል አሸነፈ

ማክሰኞ ጥቅምት 25, 2018 37

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የ4ኛ ዙር ጨዋታ አርሰናል ስላቪያ ፕራግን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
በቼክ ሪፐብሊክ በተደረገው ጨዋታ ሚካኤል ሜሪኖ ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል፡፡ አንዷን ግብ ደግሞ ቡካዮ ሳካ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል፡፡
መድፈኞቹ በሻምፒዮንስ ሊግ 4ኛ ተከታታይ ድላቸውን ሲያስመዘግቡ አሁንም መረባቸውን የሚደፍር ተጫዋችም ይሁን ክለብ አልተገኘም፡፡
በጨዋታው ተቀይሮ የገባው የ15 ዓመቱ ማክስ ዶውማን በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የተጫወተ በዕድሜ ትንሹ ተጫዋችም ሆኗል፡፡
የሰሜን ለንደኑ ክለብ በውድድር ዓመቱ ካደረጋቸው 16 ጨዋታዎች 14ቱን ሲያሸንፍ ግብ የተቆጠረበት በሦስቱ ብቻ ነው፡፡