Search

አዲሱ የኢትዮጵያ ፓስፖርት የ"ሬድ ዶት" ሽልማት አሸናፊ ሆነ

ቅዳሜ ጥቅምት 29, 2018 66

በአዲስ መልክ ሥራ ላይ የዋለው የኢትዮጵያ ፓስፖርት በልዩ ዲዛይኑ፣ በደኅንነት ባሕሪያቱ እና በመረጃ ይዘቱ እውቅና በማግኘት "ሬድ ዶት" ሽልማትን አሸናፊ ሆኗል።

ሽልማቱ በፓስፖርቱ ውስጥ ለተካተቱት ባሕሪያት በተለይም ለልዩ የመረጃ ይዘቱ እና የደኅንነት ባሕሪያቱ የተሰጠ እውቅና መሆኑ ታውቋል።

የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት በጀርመን በርሊን በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ሽልማቱን ተቀብለዋል።

ዓለም አቀፍ ውድድሩ በሦስት ዘርፎች የተከፈለ ሲሆን፤ እነሱም የይዘት ዲዛይን፣ የኮምዩኒኬሽን ዲዛይን እና የዲዛይኖቹ ፅንሰ ሀሳብ ናቸው።

ዓለም አቀፍ ደረጃውን አሟልተው የየምድባቸው አሸናፊ የሚሆኑትን የወሰኑት ዓለም አቀፍ ዳኞች መሆናቸውን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መረጃ አመልክቷል።

"ሬድ ዶት" የዲዛይን ሽልማት ለምርት እና ለኢንዱስትሪ ዲዛይን፣ ለብራንድ እና ለኮሙኒኬሽን ዲዛይን እንዲሁም ለንድፍ ፅንሰ-ሀሳቦች የሚሰጥ ዓለም አቀፍ ዓመታዊ የንድፍ ውድድር ነው።

ሽልማቱ ... 1954 ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ አርአያነት ላላቸው ምርቶች ዕውቅና እየሰጠ እንደሚገኝ ታውቋል።

በለሚ ታደሰ

#EBC #EBCdotstream #immigration #reddotaward2025 #passport