8ኛው የቻይና ዓለም አቀፍ የገቢ-ምርቶች ኤክስፖ (CIIE) የተለያዩ አዳዲስ የመጓጓዣ ምርቶች እና የፈጠራ ቴክኖሎጂዎችን በሻንጋይ ለዕይታ አቅርቧል።
አዳዲስ የአየር፣ የባሕር እና የየብስ የመጓጓዣ ቴክኖሎጂዎች የቀረቡበት ኤክስፖው ስለወደፊቱ የዓለም የመጓጓዣ ሥርዓት ዘርፈ ብዙ እይታዎች የተመላከቱበት ነው።
ሳይንደረደር መነሳት የሚችለው የኤሌክትሪክ አውሮፕላን የበርካታ ጎብኝዎችን ቀልብ የሳበ አዲስ የፈጠራ ውጤት ነው።
ጠንካራ ሆኖ በአየር እየተሞላ አገልግሎት የሚሰጥ እጅግ ቅንጡ ጀልባ፣ በራሪ ሞተር ሳይክል፣ ተጣጣፊ ጎማ የተገጠመለት ሮቦት ጫማ በኤስፖው ላይ ቀርበው የብዙዎችን አድናቆት ካገኙ ምርቶች መካከል ናቸው።
በሻንጋይ እየተካሄደ ባለው የገቢ-ምርቶች (CIIE) ቢ.ኤም.ደብልዩ የወደፊቱን የትራንስፖርት ዘርፍ ይቀይራል የተባለለት "Neue Klasse" የተሰኘ አዲስ የመጓጓዣ ቴክኖሎጂ ለእይታ አቅርቧል።
"Neue Klasse" የጀርመኑ አውቶሞቢል ኩባንያ ከቻይና የፈጠራ ባለሙያዎች ጋር በትብብር የሠራው በሲሊንደር ባትሪ የሚንቀሳቀስ "ኢ-ድራይቭ" የመቆጣጠሪያ ሥርዓት ያለው ተሽከሪካሪ ሲሆን፤ የፈጠራ ሥራው ያለቻይና የፈጠራ ባለሙያዎች ተሳትፎ የሚሳካ እንዳልነበር የኩባንያው ሊቀመንበር ኦሊቨር ዚፕስ ተናግረዋል።
ለ8ኛ ጊዜ እየተካሄደ ያለው ዓመታዊ ኤክስፖ ቻይና ከንግድ ትርዒት አቅራቢነት ወደ ፈጠራ ማዕከልነት እንድትቀየር አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን የሲጂቲኤን መረጃ ያመላክታል።
ሀገሪቱ በ‘ኢኖቬሽን ኢንዴክስ’ በ2012 ከነበረችበት 34ኛ ደረጃ በ2025 ወደ 10ኛ ደረጃ ከፍ ማለቷን የዓለም አዕምሯዊ ንብረት ድርጅት አስታውቋል።
በለሚ ታደሰ
#EBCdotstream #China #Shanghai #CIIE #innovation #mobilityproducts #expo