Search

ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

እሑድ ጥቅምት 30, 2018 270

አንጋፋው የታሪክ ምህሩና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት በ87 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ፕሮፌሰር ላጲሶ በህይወት በነበሩበት ዘመን ለሀገራቸው ኢትዮጵያ እንዲሁም ለአፍሪካ የታሪክ ጥናትና ምርምር ትልቅ አበርክቶ የነበራቸው ሲሆን፤ የተለያዩ የታሪክ መፅሀፍቶችን ፅፈው ያሳተሙና በዘርፉ አንቱታን ያገኙ ታላቅ ምሁርም ነበሩ።

ፕሮፌሰር ላጲሶ የኢትዮጵያውያንን የጋራ እሴት፣ ባሕልና ቋንቋ በማውሳት የሕዝቦች ታሪክ ጎልቶ እንዲታወቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውም ተመላክቷል፡፡

የፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ የአስክሬን ሽኝትና ቀብር ሥነ ሥርዓት የፊታችን ማክሰኛ ሕዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡