Search

የፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ’ዴሌቦ የአስከሬን ሽኝት ሥነ -ሥርዓት እየተካሄደ ነው

ማክሰኞ ኅዳር 02, 2018 263

የፕሮፌሰር ላጲሶ ዴሌቦ የአስከሬን ሽኝት ሥነ -ሥርዓት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ እየተካሄደ ነው፡፡

በሽኝት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የፕሮፌሰሩ የሥራ ባልደረቦችና ወዳጅ ዘመዶች ተገኝተዋል።

ፕሮፌሰር ላጲሶ ዴሌቦ ባደረባቸው ሕመም ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ጥቅምት 30 ቀን 2018 . ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወቃል፡፡

የታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ላጲሶ በኢትዮጵያና በአፍሪካ የታሪክ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የተለያዩ የታሪክ መጽሐፍትን ለአንባቢያን በማበርከት አገራቸውን አገልግለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የሁሉም፣ ሁሉም የኢትዮጵያ የሚለውን ነባራዊና ተጨባጭ እውነታ ይዘው ፊት ለፊት ሲሞግቱ የኖሩ ታላቅ ምሁር መሆናቸውም በህይወት ታሪካቸው ተገልጿል፡፡

ፕሮፌሰር ላጲሶ በግፍ ለተበደሉት በመሞገት፣ ከነጠላ ትርክት ይልቅ የጋራ ትርክትን አጉልተው በማሳየት የኢትዮጵያን ህዝቦች ህብረ ብሄራዊነት ሲያንጸባርቁ የኖሩ ታላቅ ምሁር እንደነበሩም ተመላክቷል፡፡

በመሀመድ ፊጣሞ