Search

ኢትዮጵያ በ2027 COP32 ጉባዔን እንድታስተናግድ ተሳታፊ ሀገራት ተስማሙ

ማክሰኞ ኅዳር 02, 2018 192

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2027 የሚካሄደውን የዓለምአየር ንብረት ጉባዔን (COP32) በአዲስ አበባ እንድታስተናግድ የጉባዔው አባል ሀገራት በመርሕ ደረጃ መስማማታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

የዘንድሮው COP30 ጉባዔ ፕሬዚዳንት አንድሬ ኮሪያ ለሮይተርስ እንደተናገሩት፥ ኢትዮጵያ ዛሬ ምሽቱን 2027 አስተናጋጅ ሆና ይፋ እንድትደረግ ሀገራት በመርሕ ደረጃ ተስማምተዋል።

ኢትዮጵያ ባሳለፍነው መስከረም ወር ጉባዔውን የማስተናገድ ፍላጎቷን ይፋ ያደረገች ሲሆን፤ የአፍሪካ ሀገራትም ኢትዮጵያ 2027 የሚካሄደውን የዓለምአየር ንብረት ጉባዔ (COP32) እንድታስተናግድ በሙሉ ድምጽ መስማማታቸውም ነው የተዘገበው።

የቀጣዩ ዓመት የዓለምአየር ንብረት ጉባዔ (COP31) አስተናጋጅ ሀገር ማንነት አሁንም ያልተለየ ሲሆን፤ አውስትራሊያ እና ቱርክ ጉባዔውን ለማስተናገድ ጥያቄ አቅርበዋል።

አውስትራሊያ COP31 ጉባዔን ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ ከሆኑ ቦታዎች መካከል ቀዳሚ ከሚባሉት የፓሲፊክ ደሴቶች ጋር በመተባበር ለማዘጋጀት ማለሟን አስታውቃለች።

በሰለሞን ከበደ

#ebcdotstream #COP30 #climate #Brazil #Belem #Ethiopia #Africa