በብራዚል፣ ቤለም እየተካሄደ ባለው የዓለም የአየር ንብረት ጉባዔ (ኮፕ30) ኢትዮጵያ እአአ በ2027 የሚካሄደውን ኮፕ32 ለማዘጋጀት በይፋ ጥያቄ አቅርባ የተሳታፊ ሀገራቱን ይሁንታ አግኝታለች።
ጉባዔውን ለማዘጋጀት ኢትዮጵያ በእርግጥም ትክክለኛዋ ምርጫ ናት፤ ለምን ቢባል፥
· ቁርጠኝነትን የተላበሰ ጠንካራ አመራር አላት
· የአፍሪካ ዲፕሎማሲ መዲና ናት
· የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ተጨባጭ እርምጃ በመውሰድ ላይ ናት
· መዲናዋ አዲስ አበባ ለኮንፈረንስ ቱሪዝም በሁሉም መስፈርት ምቹ ሆና ተዘጋጅታለች
· ጉባዔውን በኢትዮጵያ ማዘጋጀት የአፍሪካን ድምፅ በዓለም ይበልጥ ተደማጭ ያደርገዋል
· የችግሩ ዋነኛ ገፈት ቀማሾች ድርድሩን እንዲመሩት ዕድል ይሰጣል