Search

ለትውልዱ ወሳኝ የሆነው የጋራ ትርክት ግንባታ

ረቡዕ ኅዳር 03, 2018 175

የትርክቶች ሁሉ መነሻ ቃል ነው ይላሉ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስ የልማት ጥናት ዲን ዋቅጋሪ ነጋሪ (ዶ/ር)።
ቃል ደግሞ ይሰብራል፣ ይጠግናል፤ የተሻለ ሃሳብ ያለው አሰባሳቢ ትርክት ደግሞ ስብራቶችን ይጠግናል ሲሉ አስረድተዋል።
ምሁሩ ከኢቲቪ አዲስ ቀን ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ያለፉ ስህተቶቻችንን እያረምን ወደፊት በመጓዝ የጋራ ትርክትን ልንገነባ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።
የጋራ እሴቶቻችንን እና ታሪኮቻችንን አፅንተን ባለመቆየታችን አዲስ እሳቤዎችን እና ምርምሮችን እንዳናመጣ አድርጎናል ይላሉ።
ትርክትን የምንገነባው ሕዝቦችን በማሰባሰብ የተሻለ ነገር ለመፍጠር ነው የሚሉት ምሁሩ፤ እርስ በርስ ስምምነት ሲኖረን ተፅእኖ ፈጣሪነታችን እንደሚገዝፍም ነው የጠቀሱት።
ስንተባበር ኃይል እናገኛለን፤ ብሎም የውጭ ጠላቶቻችን ክፍተት አያገኙም ሲሉም አንስተዋል።
በጅማ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህር የሆኑት በላይ በየነ በበኩላቸው፤ ገዢ ትርክት በመገንባት የበለፀገች ሀገርን መገንባት ይገባል ብለዋል።
የጋራ ትርክትን ለመገንባት የሃሳብ የበላይነትን ማጠናከር እና ባህል ማድረግ እንደሚገባም ነው ያነሱት።
ያለፉ ስህተቶቻችንን እያረምን ወደፊት መጓዝ እንደሚገባም ነው የጠቀሱት።
እንደ ዓድዋ ያሉ ድሎችን ማጉላት እንደሚያስፈልግ እና ዳግም ዓድዋ የሆኑ ፕሮጀክቶቻችንን ማስቀጠል እንዳሚገባም ጠቅሰዋል።
 
 
በሜሮን ንብረት