Search

ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ኢትዮጵያ የኮፕ 32 አስተናጋጅ ስለመሆኗ ምን አሉ?

ረቡዕ ኅዳር 03, 2018 237

ኢትዮጵያ 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) እንድታስተናግድ በአፍሪካ የተደራዳሪዎች ቡድን ተመርጣለች።

ለአፍሪካ አህጉር የተሰጠውን የኮፕ32 ጉባኤ አስተናጋጅነትን ተከትሎ ኢትዮጵያ 2027 ጉባኤ ለማስተናገድ ከወዲሁ ቅድመ ማረጋገጫ አግኝታለች።

ይህንን ተከትሎም በርካታ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ስለኢትዮጵያ መመረጥ እየዘገቡ ይገኛል።

ሮይተርስ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ተደራዳሪዎች COP32 የአየር ንብረት ጉባኤን እንድታስተናግድ መመረጧ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ዲፕሎማሲ ውስጥ ያላትን አቋም ያጠናክራል ሲል ዘግቧል።

ዴይሊ ኔሽን በበኩሉ፤ ኢትዮጵያ የጉባኤው አዘጋጅ እንድትሆን መመረጧ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ሥራዎች ላይ ላበረከተቻቸው ጉልህ አስተዋጽኦዎች ዕውቅና እንደመስጠት ነው ሲል ባለሙያዎችን ጠቅሶ ገልጿል።

ኤሶሺዬትድ ፕሬስ ደግሞ፤ ኢትዮጵያ .. 2027 የሚካሄደውን ጉባኤ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፣ ይህ ውሳኔ በአፍሪካ ተደራዳሪዎች ቡድን የተደገፈ ነው ሲል አመላክቷል።

ኢትዮጵያ 2027 COP32 የአየር ንብረት ጉባኤን ለማስተናገድ የአፍሪካ ሀገራትን ድጋፍ አግኝታለች፣ ይህም ለሀገሪቱ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት መሆኑን የገለፀው ደግሞ ኒው አረብ የተሰኘው ሚዲያ ነው።

የሕንድ መገናኛ ብዙኃንም ኢትዮጵያ ኮፕ32 እንድታስተናግድ የተደረገው ውሳኔ በአፍሪካ ሀገራት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ ያለውን የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ያለውን አስቸኳይ ፍላጎት ያጎላል ሲሉ ገልፀዋል።

ፍራንስ 24 በበኩሉ፤ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች ቡድን አባላት ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ጉባኤን እንድታስተናግድ በይፋ መደገፋቸውን አንስቶ ዘግቧል።

ቲአርቲ አፍሪካ እና አፍሪካ ኔውስ ኢንተርናሽናል፤ ኢትዮጵያ ጉባኤውን ለማስተናገድ ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱ ለምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ትልቅ ድል መሆኑን ገልጸዋል።

በጌትነት ተስፋማርያም

#Ebc #Ebcdotstream #Ethiopia #COP30 #COP32 #ClimateChange