ኢቢሲ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 የባሕር በርን በተመለከተ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ቆይታ አድርጓል።
ከዚህ ቀደም በነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት አስተዳደር የባሕር በር ጉዳይን ማንሳት እንደ ጥፋት ይቆጠር እንደነበር የቦሮ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ የውጭና ዓለም አቀፍ ዘርፍ ኃላፊ መብራቱ አለሙ (ዶ/ር) አስታውሰዋል።
በተቃራኒው የአሁኑ መንግሥት ኢትዮጵያ የባሕር በር ያስፈልጋታል ብሎ በቁርጠኝነት መነሳቱ ተገቢ መሆኑንም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት እንድትሆን ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከመንግሥት ጎን በመቆም የበኩላቸውን እንዲጥሩም አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ የባሕር በር እንድታገኝ ለማድረግ መንግሥት እንቅስቃሴ ሲጀምር ጉዳዩ በመንግሥት ስለተነሳ ብቻ ማጣጣል እና መቃወም ተገቢ አይደለም ያሉት ደግሞ የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጋሻው መርሻ ናቸው።
መንግሥት የጀመረውን የባሕር በር ባለቤትነት ጉዳይ በተሻለ ፍጥነት እንዲያስፈፅም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምንችለውን ሁሉ ማገዝ ይጠበቅብናል ብለዋል ኃላፊው።
ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ላይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከመንግሥት ጎን እንዲቆሙም ጠይቀዋል።
በየተመኙሽ አያሌው
#EBC #EBCdotstream #Ethiopia #seaaccess #portaccess #seaportaccess