20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ከ2 ሳምንታት በኋላ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስተናጋጅነት ይከበራል።
በዓሉን ለማክር ከሚደረግ ዝግጅት ጋር ተያይዞ በክልሉ በብዙ መልኩ የሚገለፅ መነቃቃት መፈጠሩን ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
በርከት ካሉ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን የተውጣጣ የጋዜጠኞች ቡድን ክልሉ ከበዓሉ ጋር በተያያዘ እያከናወናቸው ባሉ የልማት ሥራዎች ዙሪያ የመስክ ምልከታ በማድረግ ላይ መሆኑን ዶ/ር እንዳሻው ጠቅሰዋል።
በክልሉ ገጠራማ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው የተነቃቃ የልማት እንቅስቃሴ የኅብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ እየቀየረው፤ በከተሞችም እየተገነቡ ያሉ መሠረተ ልማቶች ገፅታቸውን እየለወጡት ስለመሆናቸው ጠቅሰዋል።
ከተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተውጣጣው የጋዜጠኞች ቡድን በክልሉ እያደረገው ያለው የመስክ ምልከታ የክልሉን ማህበራዊ እሴቶች እና ፀጋዎች ለማወቅና ለማስተዋወቅ ምቹ አጋጣሚ መፍጠሩንም ገልጸዋል።
#ebcdotstream #centralethiopia #nationalitiesday