Search

ለሠራዊት አባላት እና ቤተሰቦቻቸው የፋይናንስ ድጋፍ መስጠት የሚያስችል የፋይናንስ ተቋም ወደ ስራ ገባ

ዓርብ ኅዳር 12, 2018 234

በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን አማካኝነት ለሠራዊት አባላት እና ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ በጡረታና በክብር ለተሰናበቱ የጦር አባላት የፋይናንስ ድጋፍ መስጠት የሚያስችለው የዓድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ወደ ስራ ገብቷል።

የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ የዓድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስን መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

ማይክሮ ፋይናንሱ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ደህንነት በማሻሻል ለሠራዊት አባላት እና ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ በጡረታና በክብር ለተሰናበቱ የጦር አባላት ቅድሚያ በመስጠት የሚሰራ ይሆናል ተብሏል።

ከሰራዊቱ ባለፈ በገጠር ሆነ በከተማ ለሚገኙ አነስተኛ ገቢ ላላቸው ስራ ፈጣሪዎች የፋይናንስ አገልግሎት ከማቅረብ ባለፈ የንግድ ማማከር አገልግሎት ጨምሮ ከ10 በላይ አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በአሁኑ ሰዓትም ካፒታሉ 678 ሚሊየን ብር የደረሰ ሲሆን 44 ሺህ 459 ባለአክሲዮኖች ይዞ በ3 ቅርንጫፎች ስራ መጀመሩ ተነግሯል፡፡

በቅርቡም በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ተጨማሪ ቅርንጫፎችን እንደሚከፍት ተመላክቷል።

የዓድዋ ድል ማይክሮፋይናንስ ስያሜውን የወሰደው የጥቁር ሕዝቦች ኩራት በሆነው ከዓድዋ ታሪክ ሲሆን፤ ማይክሮ ፋይናንሱ ስራ እንዲጀምር ያገዙ ተቋማትም በመርሀ ግብሩ ላይ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

በኤዶሚያስ ንጉሴ

#Ebc #Ebcdotstream #Ethiopia