ከህወሓት ፅንፈኛው ቡድን የጭቆና ቀንበር እና የሞት ቀጣና ሕይወታቸውን ለማዳን ያመለጡ ወጣቶች ከኢቲቪ ትግርኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ በክልሉ ያለውን ዘግናኝ እውነታ ይፋ አውጥተዋል።
ወጣቶቹ እንደሚሉት ፅንፈኛ ቡድኑ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት በግልጽ በመጣስ፣ በክልሉ የራሱን “ዘግናኝ እና የአራዊት ሕግ” ሲሉ የገለጹትን ሕግ በመደንገግ ሕዝቡ በታላቅ የጨለማ እና የፍርሃት ድባብ ውስጥ እንዲኖር አድርጎታል።
ይህ ሰላም ጠል እና ዘረኛ ቡድን ወጣቶችን ከእናቶቻቸው እቅፍ በሃይል እየነጠቀና እያገተ ወደ ማሰልጠኛና ለንግድ ወደሚሆኑ ቦታዎች እያጎራቸው ይገኛል ብለዋል።
ዛሬ ላይ ከዚህ እኩይ ተግባር ሕይወታቸውን ለማትረፍ የተሰደዱ ወጣቶች፣ መላው ሕዝብ ይህንን የቡድኑን አስነዋሪ ድርጊት በአንድ ድምፅ ሊያወግዘው እና ሊታገለው እንደሚገባ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
በአብርሃ ካሳ