ማዕከሉን መርቀው የከፈቱት የክልሉ ርዕሰ መሰተዳድ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ( ዶ/ር ) መንግስት ከዜጎች ለሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ የመስጠት ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በተለይም በመንግስታዊ አገልግሎቶች ለሚስተዋሉ እንግልቶች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት የክልሉ መንግስት በሁሉም የክልሉ ብዝሃ ማዕከል ከተሞች የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን ተደራሽ የማድረግ ሥራዎችን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አመላክተዋል።
"በማዕከሉ ለዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ ከዚህ ቀደም የነበሩ ብልሹ አሠራሮችን ማስቀረት ይቻላል" ብለዋል።
የክልሉ መንግስት በአገልግሎቶች ላይ የጀመሯቸው የሪፎርም ሥራዎች ኢትዮጵያ ለማሳካት የጀመረችውን የዲጂታል 2030ን እውን ለማድረግ የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልፀዋል።
የክልሉ መንግስት በተቋማት ግንባታ የጀመረውን ሁሉን አቀፍ ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ በበኩላቸው የማዕከሉ ሥራ መጀመር የዞኑ አስተዳደር በመልካም አስተዳደር ማዕቀፎች ትግበራ እያከናወነ ለሚገኘው ተግባር ተጨማሪ አቅምን ይፈጥራል ብለዋል።
ማዕከሉ መንግስታዊ አገልጎሎቶችን በማስተሳሰር በዜጎች ይጠየቅ ለነበረው የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጠ ይገኛል።
የማዕከሉ ሥራ መጀመር ነባራዊ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ከመፍታት ባሻገር ዜጎች ከቴክኖሎጂ ጋር ትስስር እንዲፈጥሩ ያስችላል ብለዋል።
በሰለሞን ባረና