Search

ኢትዮጵያ ታከናውናለች፡- ፈተናዎችን የተሻገረው የኢትዮጵያ የመሠረተ-ልማት ግንባታ

ሓሙስ ሰኔ 18, 2018 82

 ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ያከናወነቻቸው ግዙፍ የመሠረተ-ልማት ግንባታዎች የሀገር ውስጥ ምጣኔ-ሀብትን ከማሳደግ ባለፈ፣ የአፍሪካ ቀንድን የኢኮኖሚ ገጽታ እየቀየረ ይገኛል።

"ኢትዮጵያ ታከናውናለች" በሚለው ብሔራዊ ተስፋ እና "መደመር" እሳቤ የታገዘው ይህ ጉዞ፣ ሀገራችንን የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ማዕከል ማድረጉን ቀጥሏል።

በተለይም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያ በመሠረተ-ልማት ረገድ ካስመዘገበቻቸው ስኬቶች የኢነርጂ ሉዓላዊነት እና "አረንጓዴ ወርቅ" ሽግግር ተጠቃሽ ነው።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁ እና በሙሉ አቅም ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ለሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች አስተማማኝ ግብዓት ከመሆን ባለፈ፣ ለጎረቤት ሀገራት በተለይም ለሱዳን፣ ጅቡቲ እና ኬንያ የሚላከውን የኃይል መጠን አሳድጎታል።

ይህ ንፁህ ታዳሽ ኃይል ሀገራችንን ከካርቦን ሽያጭ የምታገኘውን ገቢ የሚያሳድግ እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የምታደርገውን የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄን በምጣኔ-ሀብት የሚያጠናክር ነው።

ሌላው የትራንስፖርት እና የኮሪደር ልማት ሥራዎች ሲሆኑ፣ በዚህም ከአዲስ አበባ - ጅቡቲ የባቡር መስመር ባሻገር፣ ኢትዮጵያን ከኬንያ በሞያሌ በኩል እና ከሌሎች ጎረቤቶች ጋር የሚያገናኙ ዘመናዊ አውራ ጎዳናዎች ተገንብተዋል። ይህም የኢትዮጵያን "ቅድሚያ ለጎረቤት" የዲፕሎማሲ ፖሊሲ በተግባር ያሳየ ነው።

የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች በዋና ዋና ከተሞች በተለይም በአዲስ አበባ የተከናወኑት የኮሪደር ልማት ሥራዎች የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ፣ የንግድ እንቅስቃሴን ያቃለሉ እና የከተማ ኑሮ ደረጃን ያሻሻሉ ናቸው።

ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ ያከናወነቻቸው ተግባራት ለዘርፉ ስኬታማነት ትልቁን ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ። በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ቀዳሚነቱን ሚና በመያዝ በሀገር ውስጥ የአውሮፕላን ማረፊያ መመሠረተ-ልማቶችን በማስፋፋትና አዳዲስ የጭነት ተርሚናሎችን በመገንባት የዓለም አቀፍ ንግድ ድልድይነቱን በማጽናት ላይ ይገኛል።

የዲጂታል መሠረተ-ልማት አብዮት ሌላኛው የኢትዮጵያ ስኬታማ ስራዎች ማሳያ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ያደረገችው የፖሊሲ ማሻሻያ እና የገበያ ክፍትነት፣ የዲጂታል መሠረተ-ልማቱን ፈጣን አድርጎታል።

5G ኔትወርክ መስፋፋት፣ የዳታ ማዕከላት መገንባት እና የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶች እንደ -ብር እና ቴሌብር ያሉ መስፋፋት ሀገራችንን ለዲጂታል ኢኮኖሚ ዝግጁ አድርገዋታል።

ይህም የሚያሳየው የኢትዮጵያ የመሠረተ-ልማት ጉዞ የሀገር ግንባታ፣ የኢኮኖሚ ሪፎርም እና የትውልድ ቅብብሎሽ መሆኑን ነው። ፈተናዎች ቢኖሩም፣ የተዘረጉት መሠረተ-ልማቶች ለሀገራችን ዕድገት የማይናወጥ መሠረት ጥለዋል፤ እየጣሉም ይገኛሉ።

በአድማሱ አራጋው