ዓመታዊው የብሔራዊ ደኅንነት ኮንፍረንስ በአሁናዊ የሀገሪቱ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ በማተኮር እየተካሄደ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ ያዘጋጀው ዓመታዊ የብሔራዊ ደኅንነት ኮንፍረንስ መካሄድ ጀምሯል።
መድረኩ በአሁናዊ የኢትዮጵያ የብሔራዊ ደኅንነት ተግዳሮቶች እና ዘላቂ የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ይመክራል ፡፡
የብሔራዊ መከላከያ ኮሌጅ በየዓመቱ የሚያዘጋጀው ይህ የደህንነት ኮንፍረንስ መድረክ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ወታደራዊ አመራሮችና የፖሊሲ አውጪዎች ተገኝተዋል።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ወታደራዊ አማካሪ እና የተኩስ አመራር ኃላፊ ጀነራል አለምሸት ደግፌ፣ የመከላከያ የትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ጀነራል ይመር መኮንን፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ቀነአ ያደታ (ዶ/ር)፣ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ ( ዶ/ር )፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ዘሪሁን አበበ በተገኙበት እየተካሄደ ነው::
በወንደሰን አፈወርቅ