ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እንደ ሌሎች ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ ውድድሮች ይበልጥ ተጠቃሽ እና ተተኪዎችን ጭምር የምናፈራበት እንዲሆን ይበልጡኑ አበክሮ ይሠራል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፤ ተወዳጁን፣ ተናፋቂውን እና ባለፉት 25 ዓመታት የከተማችን አንዱ ድምቀት እና አለም አቀፍ መገለጫ የሆነውን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያን በልዩ ድምቀት አስጀምረናል ብለዋል።
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የዓለም ኮከብ አትሌቶች መለማመጃ፣ መኖሪያ በሆነችው መዲናችን አዲስ አበባ፣ ከልጅ እስከ አዋቂ፣ ከፕሮፌሽናል አትሌት እስከ ጤና ቡድኖች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ እየተሳተፈበት፣ እየተዝናናበት፣ ጤናውን እየጠበቀበት፣ ወንድማማችነትን፣ እህትማማችነትንና አብሮነትን እያጠናከረበት 25 የድምቀት ዓመታትን አሳልፏል ሲሉም ገልፀዋል።
የዚህ ታላቅ ውድድር መስራች የሆነውን ጀግናው አትሌታችንን ሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴን፣ እንዲሁም አጠቃላይ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አመራሮችን ባለሙያዎችን እና አስተባባሪዎችን ለዘመን ተሻጋሪ ሥራችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል።
ተሳታፊዎች፣ የፀጥታ አካላት፣ በጎ ፈቃደኞች፣ የሚዲያ ባለሙያዎች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ለውድድሩ ስኬት ለነበራችሁ በጎ አስተዋፅኦ ከልብ አመሰግናለሁ ሲሉም ገልፀዋል።
#Ebc #Ebcdotstream #Ethiopia #GreatEthiopianRun #AddisAbaba