Search

ዛሬ የተጀመረው ሀገር አቀፍ የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት

ማክሰኞ ኅዳር 16, 2018 82

ህጻናት  እንደተወለዱ የሚሰጠው ሀገር አቀፍ የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአበበች ጎበና የእናቶችና ህጻናት ሆስፒታል ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ የተገኙት የጤና ሚስትር ዴዔታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ፥ ህጻናት ጤናማ እና ብቁ ዜጎች እንዲሆኑ እንደተወለዱ በ24 ሰዓት ጊዜ ውስጥ ክትባቱን ማግኘት አለባቸው ብለዋል።

የጉበት በሽታ ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴዔታው ለመከላከያ ክትባቱ ሁሉም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል።

የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባቱ ከዛሬ ጀምሮ በመደበኛ ክትባት መርሐ ግብር ተካትቶ መሰጠት እንደሚጀምርም ዶ/ር ደረጀ ገልጸዋል።

የጤና ሚኒስቴር በ2030 ሁሉም እናቶች በጤና ተቋም እንዲወልዱ ለማድረግ አቅዶ እየሠራ መሆኑም ተገልጿል።

በፕሮራሙ ላይ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች፣  የዓለም የጤና ድርጅት ተወካዮች እና የዘርፉ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

በመሐሪ ዓለሙ

#ebcdotstream #hepatitis #vaccine