Search

ኢትዮጵያ ለምታዘጋጀው ኮፕ 32 ቁልፍ የዝግጅት ተግባራትን ለማቀናጀት የሚያስችል የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ ተደረገ

ሓሙስ ኅዳር 18, 2018 60

በትናንትናው ዕለት የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዚዳንት መሰየምን ተከትሎ ዛሬ ጠዋት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ቁልፍ የዝግጅት ተግባራትን ለማቀናጀት የሚያስችል የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ ተደርጓል።
ስብሰባው ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን ስታስተናግድ አካታች እና በሚገባ የተሰናዳ ጉባኤ እንድታሳካ ለማረጋገጥ መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት እንደነበር የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።