Search

ክብረ በዓሉ የኢትዮጵያን ብዝኀ መልክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ይረዳል - አፈጉባዔ አቶ አገኘሁ

ቅዳሜ ኅዳር 27, 2018 85

በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር የተመራ የልዑካን ቡድን በ20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል የማጠቃለያ መርሀ ግብር ላይ ለመሳተፍ ሆሳዕና ከተማ ገብቷል።
አፈ-ጉባዔው እና የልዑካን ቡድኑ ሆሳዕና ከተማ ሲደርሱ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ፣ በክልሉ አፈጉባዔ ወ/ሮ ፋጤ ሰርሞሎ በክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ በአገር ሽማግሌዎች፣ በሃይማኖት መሪዎች፣ በከተማ አመራሮችና በነዋሪዎች ደማቅ አቀባባል ተደርጎላቸዋል።
 
አቶ አገኘሁ ተሻገር የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል መከበር የኢትዮጵያን ብዝኀ መልክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል።
በተጨማሪም ክብረ በዓሉ፤ ባህላዊ እሴቶችን፣ መልካም ተሞክሮዎችንና ልምዶችን ለመለዋወጥ፣ ኅብረብሔራዊና ዲሞክራሲያዊ አንድነትን ለማጠናከር ከሚኖረው ፋይዳ ባሻገር ለከተማዎች ሁለንተናዊ መነቃቃትና እድገት፣ ለቱሪስት መስህብነት የሚኖረው አስተዋጽኦ ጉልህ መሆኑን ተናግረዋል።
በ20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በፌዴሬሽን ምክር ቤት አስተባባሪነትና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ አስተናጋጅነት “ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ እንደሚከበር ይታወቃል።
 
በመስከረም ቸርነት