ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 6 ሺህ 492 ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት መስኮች እና ደረጃዎች አስመርቋል።
በምርቃቱ ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ ተመራቂዎች የዋንጫ እና የሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል።
ከተመራቂዎች መካከል በቢዝነስ ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ የትምህርት መስክ የተመረቀው ተማሪ እዝራ አንዱዓለም በዩኒቨርሲቲው ከወሰዳቸው አጠቃላይ የትምህርት መስኮች መካከል 43ቱን ‘A+’ እና ዘጠኙን ‘A’ በማምጣት ሙሉ 4 ነጥብ ማስመዝገብ ችሏል።
ባለ ብሩህ አዕምሮው ተመራቂ እዝራ ዋንጫውን ከክብር እንግዳው እጅ ተቀብሏል። ተመራቂው ባደረገው ንግግር ለተመራቂዎች እና ቤተሰቦቻቸው በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል።
ዛሬ ላይ የሚያስደስት እና የተመቻቸ ሕይወት ላይኖር ይችላል፣ ነገር ግን በብርታት እና በተስፋ መቀጠል ይኖርብናል ነው ያለው።
ለዚህ ምርቃት ስንበቃ በኹሉም ነገር በቅተን አለመሆናችንን መገንዘብ ያስፈልገናል፤ ይልቁንስ ወደፊት ትምህርታችንን ቀጥለን ብቁ ተማሪዎች መሆናችንን መቀጠል እንዳለብን መዘንጋት አይገባንም ብሏል።
በቀጣይም ትምህርታችንን ቀጥለን ማንኛውም እናት እና ሀገር የምትኮራበት እንድንሆን ተግተን መሥራት ይገባናል ነው ያለው።
ስኬታማ እንዲሆን ያገዙትን ሁሉ ማመስገኑን አሚኮ ዘግቧል።