Search

48 'A+' ያስመዘገበው ባለ ብሩህ አዕምሮ ተማሪ

ቅዳሜ ሰኔ 20, 2018 363

በሪሳ ሹሌ የተባለው የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በኤሌክትሪካል እና ኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ የትምህርት ክፍል 48 'A+' በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

ተመራቂው ከ62 የትምህርት ዓይነቶች መካከል 48ቱን 'A+'፣ 12ቱን 'A' እንዲሁም 3ቱን 'A-' በማምጣት በጠቅላላ ነጥብ (CGPA) 3.98 ሊመረቅ ችሏል።

በተጨማሪም በሀገር አቀፉ የሙያ ብቃት ምዘና ፈተና (Exit Exam) ከመቶ 92 ማስመዝገቡ ታውቋል።

በሪሳ ለዚህ ታላቅ ስኬት የበቃበትን ምስጢር ሲናገር፤ ጊዜውን በአግባቡ በመጠቀም እና በሥርዓት ማጥናቱ እንደሆነ መግለጹን ኦቢኤን ዘግቧል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: