ኢትዮጵያ የሚያዋጣትን የኅብረ ብሔራዊነት መንገድ መምረጧን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ።
20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን ለማክበር የተመረጠው መሪ ቃል "ዴሞክራሲያዊ መግባባት፣ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት" የሚል መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም ተሻጋሪነት ያለው እና ልንኖረው የሚገባ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት 60 ዓመታት ሲጠየቁ ከነበሩት ጥያቄዎች መካከል ዴሞክራሲ እና ብዝኃነት በመሪ ቃሉ ውስ መካተታቸውን አውስተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን ስናከብር ስለወል ትርክት ማሰብ ይገባናል ብለዋል ዶ/ር እንዳሻው።
የወል ትርክት ወደፊት ለመጓዝ አቅም ሲሆን፤ ነጠላ ትርክት ግን አቅምን የሚበላ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የሚበጀውን የጋራ መንገድ መፍጠር እንደሚገባም ነው ገለጹት።
ያደጉ ሀገራት ዋነኛው ጥንካሬያቸው የጋራ አጀንዳዎችን ፈጥረው በጋራ መሥራታቸው ስለመሆኑ ጠቅሰው፣ ኢትዮጵያም ኅብረ ብሔራዊነቷን አጠናክራ ወደፊት ለመንደርደር እየሠራች ነው ብለዋል።
በለሚ ታደሰ
#ebcdotstream #Ethiopia #nationalitiesday #hosaena