Search

የኢትዮጵያ ማዕከላዊነት የሁላችን መሻት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሰኞ ኅዳር 29, 2018 81

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ እየተከበረ በሚገኘው 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል ላይ ንግግር አድርገዋል።

ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የዛሬውን በዓል ያዘጋጀው እና ኢትዮጵያን ያሰባሰበውን ሀዲያን አመስግነዋል።

ኢትዮጵያ አንዱ ከፍ ሌላው ዝቅ የሚልባት ሳይሆን ሁላችን የምንደምቅባት ነች ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ኢትዮጵያ በሁሉም መመዘኛ ወደ ብርሃን አየተሸጋገረች ባለችበት ወቅት እንዲህ መሰባሰባችን ታሪካዊ ነው ያሉት ጠቅላይ ማኒስትሩ፤ ብርሃኑን ለማጉላት በኅብረት መቆም አለብን ብለዋል።

ኢትዮጵያን ችግሯን ብቻ ሳሆን አቅሟን ማየት እንሚገባ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ልጆቿ በጠንካራ አንድነት በጋራ ከቆሙ ከፍታዋን ማረጋገጥ ይቻላል ነው ያሉት።

እንደ ድር አብረን ለነገ ትውልድ የምትመች ኢትዮጵያን በጋራ እንሥራ በማለትም ጥሪ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ የጀመረችውን አስደናቂ ጉዞ ለማስተጓጐል እንቅልፍ የሚያጡ ቢኖሩም ኢትዮጵያን ከጉዞዋ አያቆሟትም ብለዋል።

የኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ ልጆች አንሸማቀቅም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ተምሳሌት ሆና ትቀጥላለች ሲሉ ተናግረዋል።

"ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት'' በሚል መሪ ሐሳብ እየተከበረ በሚገኘው በዓል ላይ፤ ከመላው ኢትዮጵያ የመጡ የብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የከማ አስተዳዳሮች ከንቲባዎች እና የፌዴራል ከፍተኛ አመራሮች በበዓሉ ላይ ተገኝተዋል።

በለሚ ታደሰ

#Ebc #Ebcdotstream #Ethiopia #nationnationalityday #PMAbiy