ጅማ ከተማ 21ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል እንድታዘጋጅ በይፋ ተመርጣለች፡፡
20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓል “ዴሞክራሲያዊ መግባባት፣ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሆሳዕና ከተማ እየተከበረ ይገኛል።
በስነ ስርዓቱ ላይም ጅማ ከተማ በቀጣይ ዓመት የሚከበረውን 21ኛውን የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል እንድታዘጋጅ ተመርጣለች፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የዝግጅቱን ሰንደቅ ዓላማ ለኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አስረክበዋል፡፡
በሜሮን ንብረት
#Ebc #Ebcdotstream #Ethiopia #nationnationalityday