Search

እኩልነት እና ወንድማማችነት የጎለበቱበት የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል

ሰኞ ኅዳር 29, 2018 56

የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል እኩልነትንና ወንድማማችነትን በሚያጎለብቱ፣ ዘላቂ ሰላምንና ሁለንተናዊ ብልጽግናን በሚያፈጥኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ታጅቦ ሲከበር ቆይቷል ሲሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ እየተከበረ ነው።
በዚህ ወቅት ንግግር ያደረጉት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፤ ባለፉት 19 ዓመታት በዓሉ ሲከበር መቆየቱን አስታውሰው፣ ይህም በሕዝቦች ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ላይ ውጤት እንዲመጣ አስችሏል ብለዋል፡፡
አክለውም የህዝብ ለህዝብ ትሥሥር፣ ወንድማማችነትን እና አብሮ የመኖር እሴትን በማጠናከርም የሀገረ መንግሥት ግንባታ ሂደቱን በማፋጠን በኩል ትልቅ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡
በዓሉ ሁሉም ማንነቶች እኩል የሚስተናገዱበት እውነተኛ የፌዴራል ሥርዓት በመገንባት ሂደት አዲስ የታሪክ እጥፋት ላይ መሆናችንን የምናሳይበት ነው ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም ከኩስመና ዘመን ወደ ማንሰራራት፤ ከቁዘማ ወደ መነቃቃት፤ ከጨለማ ወደ ተስፋ ብርሃን የተሸጋገርን መሆኑን የምንስመሰክርበት ነው ብለዋል፡፡
በመሐመድ ፊጣሞ