Search

ኢትዮጵያን ለማፅናት በጋራ እንቁም፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሰኞ ኅዳር 29, 2018 67

ኢትዮጵያን ለማፅናት በጋራ እንቁም ሲሉ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጥሪ አቀረቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ዛሬ እያከበርን ያለነው በዓል ዳግም ቃል ኪዳናችንን የምናድስበት ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን እኩል ሆነን በመደመር እሳቤ የበለፀገች ኢትጵያን ለልጆቻችን ልናሻግር ይገባል ብለዋል፡፡
ስለሆነም የጀመርነውን ለመጨረስ፤ ያልጀመርነውን ደግሞ ለመጀመርና ኢትዮጵያን ለማፅናት በጋራ እንቁም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
መሬት ከክረምት እስከ በጋ በማረስ ከምግብ ጥገኝነትን ለመላቀቅ መላው ኢትዮጵያውያውን በተለይም አርሶ አደሮች እየተጉ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን የማዕድን ሀብታችን እየተገለጠ፣ የቱሪዝም ሀብቶቻችን እያበቡ፣ ቴክኖሎጅን የመጠቀም አቅማችንም እየሰፋ እና ልምምዱም እያደገ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
በዚህም ሀገራችን ከጨለማ ወደ ንጋት እየተሸጋገረች ትገኛለች ብለዋል፡፡
20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓል "ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት'' በሚል መሪ ሃሳብ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ተከብሯል።
በየተመኙሽ አያሌው