Search

“ሰላማዊ ንግግርን እና ብሔራዊ ጥቅምን ማስቀደምን አደራ እላለሁ” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሰኞ ኅዳር 29, 2018 63

“ሰላማዊ ንግግርን እና ብሔራዊ ጥቅምን ማስቀደምን አደራ እላለሁ” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አዘጋጅነት ዛሬ በሆሳና ከተማ በተከበረው 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ላይ ባስተላለፉት መልዕክት።

ባዳ በክፋት መሻታችንን ለማጨለም ሲነሳ፤ ኢትዮጵያውያን ለባዳ ፍላጎት መሳሪያ ልንሆን አይገባም፤ ምክንያቱም በባዳ የተጠለፈ ገመድ አይፈታም፣ አያስርምና ብለዋል።

ክፉ እሳቤ ያለውን የባዳን መሻት በውስጣችን እንዳናስገባ እና በታሪክ ተወቃሽ እንዳንሆን እጅ ለእጅ እንያያዝ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያውያን ቀልብ ገዝተን በንግግር በማመን እና ሰላማችንን በማጽናት በተሰማራንበት የሥራ መስክ ሁሉ ተግተን መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

ሌብነትን በመጠየፍ፣ የሀገራችንን ጥቅም እና የሕዝባችንን ክብር በማስቀደም፣ ለለውጥ እና ለዘመናዊነት ክፍት መሆን ይገባናል ሲሉ ጠቁመዋል።

በሁሉም መስክ ሉዓላዊነታችንን በማረጋገጥ ልመናን ታሪክ ለማድረግ የጀመርነውን መልካም ጅማሮ ማስቀጠል እንዳለብንም አመላክተዋል።

ይህን ጅማሯችንን ለማደናቀፍ ሙከራዎች ይደረጋሉ፤ ነር ግን ማንኛውም ትንኮሳ እና ክፉ ሀሳብ ኢትዮጵያን ከብልፅግና ጉዞዋ ሊያቆማት አይችልም ብለዋል።

ኢትዮጵያ በብዙ ተስፋ የተሞላች እና እያንሰራራች ያለች ሀገር ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ “ሰላማዊ ንግግርን እና ብሔራዊ ጥቅምን ማስቀደምን” አደራ ብለዋል።

በሜሮን ንብረት

#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #nationalitiesday #abiyahmedali