Search

የፈጠራ አቅም ያለው ሰው ውድቀት አይፈራም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሰኞ ታኅሣሥ 13, 2018 39

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ለማብሰር በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

እንደዚህ ዓይነት መድረኮች ሌላ ጊዜ ዕድል ማግኘት የማይችሉ የፈጠራ ሀሳብ ባለቤቶች ዕድል የሚያገኙባቸው ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የፈጠራ ሀሳብ ከሌላው ተራ ሀሳብ በጣም የተለየ እንደሆነ ተናግረዋል።

በስትራቴጂ እና ማሰላሰል የተደገፈ የፈጠራ ሀሳብ የራሱ የሆነ ባሕሪ እንዳለው ጠቅሰው፤ እንደዚህ ዓይነቱ ሀሳብ ከሌላው ተሽሎ መገኘትን፣ ተከታታይ ሙከራን ማድረግን እና ውድቀትን አለመፍራትን የሚጠይቅ እንደሆነ ገልጸዋል።

የዚህ ዓይነቱ አቅም ያለው ሰው ውድቀት ቢያጋጥመው እንኳን የፈጠራ ችሎታውን ስለሚተማመን፤ ውጤታማ ባይሆን እንኳን ተስፋ ሳይቆርጥ ፈጠራው ተቀባይነት እስከሚያገኝ እንደሚሠራ አብራርተዋል። 

መንግሥትዲጂታል ዘርፉ የፈጠራ ባለቤቶችን እንደ አጋዥ እንጂ እንደ ተግዳሮት እንደማይመለከታቸው ጠቁመው፤ መንግሥት አንዳንድ አገልግሎቶች ላይ የሚገባው ክፍተቶችን ለመሸፈን እና የወድድር መንፈሱን ለማጠናከር እንደሆነ ገልጸዋል።

በዲጂታል ዘርፉ ተመሳሳይ የፈጠራ ውጤቶች ሥራ ላይ በዋሉ ቁጥር ተጠቃሚው አማራጭ እንዲያገኝ ከማድረጉም ባሻገር የፈጠራ ባለቤቶቹ ተባብረው የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ ዕድል የሚፈጥር ሊሆን እንደሚችልም ጠቁመዋል።

በለሚ ታደሰ

#EBC #EBCdotstream #DigitalEthiopia #DigitalEthiopia2030