በአማራ ክልል የፀጥታ ችግሩ ካጋጠመ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት መንግሥት የሰላም ጥሪዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል።
ይህንንም ተከትሎ በክልሉ በርካታ ታጣቂዎች የኃይል አማራጭን በመተው እና የሰላም ጥሪውን በመቀበል ወደ መደበኛ ሕይወታቸው ተመልሰዋል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን የሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አዱኛ አዳሙ፣ በዚህ ዓመት 418 ታጣቂዎች የሰላም አማራጭ መከተላቸውን ገልጸዋል።
የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች የተሃድሶ ሥልጠና እንዲወስዱ በማድረግ መደበኛ ሕይወታቸውን መጀመራቸውንም ጠቅሰዋል።
አሁን ላይ በተለያዩ ዘርፎች በመሠማራት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው፣ ኅብረተሰቡ በየጊዜው የሰላም ሁኔታው እንዲረጋጋ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመቀናጀት ትልቁን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።
አሁንም የሰላም በሩ ክፍት መሆኑን አንስተው፣ ይህን በማይቀበሉ ታጣቂዎች ላይ ሕግ የማስከበር ሥራው በተጠናከረ መንገድ እንደሚቀጥል መናገራቸውን አሚኮ ዘግቧል።

